Ethio Engineering Group

ስለ እኛ

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (EEG) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 475/2013 መሠረት በመስከረም 2013 ዓ.ም እንደ የመንግስት ልማት ድርጅት እንደገና የተቋቋመ አምራች ተቋም ነው።

እንደገና የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን በመገንባት በሀገሪቱ የኢንዱስትሪ መሠረት ያለው ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ሚና መጫወት እንዲችል ነው።

በመሆኑም ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በግብርና ማሽነሪዎች፣ ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ የኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ፣ ማሰራጫና መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፣ የብረታ ብረት ውጤቶች እንዲሁም የፕላስቲክና ኮምፖዛይት ምርቶች ዘርፍ የተሰማራ አምራች ተቋም ነው።

ግሩፑ በሀገራዊና ዓለማቀፋዊ የነፃ ገበያ ህጎች የሚመራ ሲሆን፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ አምራቾች ጋር በመተባበር በጋራ የሚሠራ ተቋም ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአገራችን የቴክኖሎጂ እድገት ጉልህ ድርሻ ያላቸው የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርቱ፣ የራሳቸው የማምረቻ ፋሲሊቲዎች ያላቸው ሰባት ኢንዱስትሪዎችን ያቀፈ ተቋም ነው።

ራዕይ

በ2022 ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕን የሚተማመኑበት አምራችና የዘርፉ የልሕቀት ምህዋር ማድረግ

ተልዕኮ

  • የአምራች ኢንዱስትሪውን እና የአገልግሎት ዘርፉን ዕድገት የሚያፋጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ማበልፀግና ማስተላለፍ
  • ከፍተኛ የገበያ ክፍተት ያስከተሉ፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁና ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ልማት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ እያመረቱ መተካት
  • የማምረቻና አገልግሎት መሰጫ ፕላንቶችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት፣ መገንባት፣ ማደስና ማሻሻል
  • የምናመርታቸውን ምርቶችና የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ለውጭ ገበያ ተደራሽ ማድረግ

ዓላማ

  • በአምራች ኢንዱስትሪዎች ፈጣን ልማት የሚያስይዙ ተጨባጭና የወደፊት ፍላጎቶችን በማጥናትና በማልት ምርትና አገልግሎትን የሚያሳልጡ የቴክኖሎጂ ሽግግር መፍጠርና አቅም ማጎልበት።
  • በኢትዮጵያ የስነ ሃብታዊና ማህበራዊ እድገት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ እና የገበያ ክፍተትን ለመሙላት የሚረዱ ልዩ ልዩ የካፒታልና የፍጆታ እቃዎችን እንዲሁም መለዋወጫዎችን ማምረት፣ መጠገን፣ ማደስና ማሻሻል።
  • የማምረቻ ወይም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት (ፕላንቶችን) ዲዛይን ማድረግ፣ መገንባት፣ ቅድመ ምርት ሙከራ እና ፍተሻ (ኮሚሽኒግ) አገልግሎት መስጠት፣ መጠገን፣ ማደስና ማሻሻል።
  • ምርትና አገልግሎቶቹን በአገር ውስጥና በውጭ አገራት መሸጥ እና የድህረ ሽያጭ አገልግሎቶችን በተጠናከረ መንገድ መስጠት።
  • በተሰማራበት የማምረቻ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠናና የማማከር አገልግሎት በመስጠት በዘርፉ የሰው ኃይል ልማት ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ።
  • የገንዘብ ሚኒስቴር የሚሰጠውን የፖሊሲዋች አቅጣጫና የማያወጣውን መመሪያ መሠረት በማድረግ ቦንድ መሸጥ፣ ዋስትና ማስያዝ፣ ከአገር ውስጥና ከውጪ አገር የገንዘብ ምንጮች የብድር ውል መደራደርና መፈረም
  • ግሩፑ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ በማድረስ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን ማከናወን
  • ኢትዩ-ኢንጂነሪንግ ግሩች የፌዴራል መንግስትን ስተራቴጂ እቅድ መነሻ በማድረግ ያቅዳል ግሩፑ ፖርትነር ሽፕ ለእድገቱ ቁልፍ ነው ብሎ ያምናል የኛ የሥራ አጋሮች ደንበኞቻችን፣ ሰብኮንትራክተሮች እና አቅራቢዋቻችን ሲሆኑ ቀጣይነት ላለው እድገት እና ለጋራ ስኬት ወሳኝ ነው፡፡

ክቡር አብርሀም በላይ (ዶ.ር)

ክቡር አብርሀም በላይ (ዶ.ር)

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር
ክብርት ወ.ሮ መሰረት መስቀሌ

ክብርት ወ.ሮ መሰረት መስቀሌ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
ክቡር ዶ.ር ዲንሰፋ መንሱር (ተባባሪ ፕሮፌሰር)

ክቡር ዶ.ር ዲንሰፋ መንሱር (ተባባሪ ፕሮፌሰር)

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪና መምህር
ክቡር በለጠ ስራህብዙ (ዶ.ር)

ክቡር በለጠ ስራህብዙ (ዶ.ር)

በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ዲፓርትመንት ተባባሪ ፕሮፌሰር
ክቡር  አቶ ደበሌ ቃበታ

ክቡር አቶ ደበሌ ቃበታ

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮምሽነር
ክቡር  አቶ አየለ ከበደ

ክቡር አቶ አየለ ከበደ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ ተመራማሪና መምህር
ክቡር አቶ ፍቅረስላሴ  ዘውዱ

ክቡር አቶ ፍቅረስላሴ ዘውዱ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ም.ፕሬዚዳንት - ክሬዲት ዘርፍ
ክቡር  አቶ ጌታቸው ዋቄ

ክቡር አቶ ጌታቸው ዋቄ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት- ኮርፖሬት አግሪካልቸር ፋይናንስ
ክቡር  አቶ ከበደ ገለታ

ክቡር አቶ ከበደ ገለታ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የዋና ሥራ አስፈፃሚ አማካሪ
ክብርት ወ.ሮ ያስሚን ወሀብረቢ

ክብርት ወ.ሮ ያስሚን ወሀብረቢ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
ክቡር አቶ አንዷለም ሲዓ

ክቡር አቶ አንዷለም ሲዓ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬት ፕላኒንግ ስራ አስፈፃሚ
አቶ አስማማው አሰፋ

አቶ አስማማው አሰፋ

በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የፕላንት ማሽነሪ ጥገና እና ክትትል ድጋፍ ቡድን መሪ
ሸጋው ሙሉጌታ

ሸጋው ሙሉጌታ

ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ዳንኤል ኦላኒ መኮንን

ዳንኤል ኦላኒ መኮንን

ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ
አብዱልፈታህ ሼክ ቢሂ (PHD)

አብዱልፈታህ ሼክ ቢሂ (PHD)

ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ የምርምርና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ
ግርማ አለማር አደከም

ግርማ አለማር አደከም

ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና ኦፕሬሽን ዘርፍ
መልዕክት