Ethio Engineering Group

ኢንዱስትሪዎች

የእኛ ቁልፍ ኢንዱስትሪዎች እና ፋብሪካዎች

አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ

የኢንዱስትሪው አመሰራረትና ታሪክ

አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተመሰረተው በ1976ዓ.ም ሲሆን፣ መጠሪያውም ናዝሬት ትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ይባል ነበር።

በ2003ዓ.ም በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሲጠቃለል አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ተብሎ ተጠራ። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 475/2020 መሰረት በ2012ዓ.ም ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እንደ አዲስ ሲቋቋም፣ በስሩ ከሚገኙ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች አንዱ ሆኖ ተቋቋመ።

ተልዕኮ

  • የእርሻ መሳሪያ ዘርፉን የሚያፋጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ማበልፀግና ማስተላለፍ
  • ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የሚፈልጉ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት
  • የእርሻ መሳሪያ ማምረቻ ፕላንቶችን ዲዛይን፣ መገንባት፣ ማደስና ማሻሻል
  • ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለውጭ ገበያ ተደራሽ በማድረግ የኤክስፖርት ድርሻ ማሳደግ

ፋብሪካዎቹ

የትራክተር ምርት ፋብሪካ
የትራክተር ተቀጽላ ማምረቻ ፋብሪካ
የውሃ ፓምፕ ፋብሪካ

የምርት ዓይነቶች

  • የተለያየ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ትራክተሮች
  • የትራክተር ተቀጽላዎች (ማረሻ፣ መከስከሻ፣ ጋሪ/ተሳቢ)
  • በናፍጣ የሚሰሩ የውሃ ፓምፖች (የተለያየ አቅም)

የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የዱቤና የእጅ በእጅ ሽያጭ
  • ጥገና
  • ስልጠና
  • የመለዋወጫ አቅርቦት

አዲስ ማሽን እና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ

አዲስ ማሽን እና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ

አዲስ ማሽን እና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በ1945ዓ.ም የተመሰረተ ኢንዱስትሪ ሲሆን፣ ዋናው መ/ቤት በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ይገኛል። የብሬክ ፓድ ማምረቻ ፋብሪካው በአፋር ክልል አዋሽ አርባ ይገኛል።

ኢንዱስትሪው በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር በነበረበት ወቅት “ህብረት ማኑፋክቸሪንግና ማሽን ማምረቻ ኢንዱስትሪ” ተብሎ ይጠራ ነበር። በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 475/2020 መሰረት በ2012ዓ.ም ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እንደ አዲስ ሲቋቋም መጠሪያ ስሙ “አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ” ተብሎ ተሰየመ እና በግሩፑ ስር ከሚገኙ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች አንዱ ሆኖ ተቋቋመ።

ተልዕኮ

  • የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪውን እድገት የሚያፋጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ማበልፀግና ማስተላለፍ
  • ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚፈልጉ የሀገር ውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ለሀገር ኢኮኖሚ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረግ
  • የማምረቻና የአገልግሎት ፋብሪካዎችን መንደፍ፣ መገንባት፣ ማደስና ማሻሻል
  • ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለውጭ ሀገር ተደራሽ በማድረግ የሀገሪቱን የውጭ ንግድ ድርሻ ማሳደግ

ፋብሪካዎቹ

ማሽን ቦዲ
ኮንቬንሽናል
ፕሪሲዥን
ማሽን ቢልዲንግ
ቦልት፣ ነትና ማቴሪያል ትሪትመንት

የምርት ዓይነቶች

  • ኢንዱስትሪያል ማሽኖች
  • መለዋወጫዎች
  • የፍሬን ሸራ
  • ቦልትና ነት
  • ሞልድና ዳይ
  • ቤሪንግና አክቹየተር

የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • ፕላንት ተከላና ዝርጋታ
  • ጥገና
  • ስልጠና
  • ማቴሪያል ቴስቲንግ
  • ሂት ትሪትመንት

ኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ

የኢንዱስትሪው አመሰራረትና ታሪክ

የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ቀደም ሲል በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር በንዑስ ኢንዱስትሪነት ሲተዳደር ቆይቶ በ2004 ዓ.ም. እራሱን በመቻል የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ውስጥ ካሉ ኢንዱስትሪዎች መካከል አንዱ በመሆን ተቋቁሟል።

ኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በመባል የተሰየመ ሲሆን፣ በ2007 ዓ.ም. ኮንስትራክሽንና ኢንጂነሪንግ ማሽነሪ ኢንዱስትሪ ተብሎ ተጠርቷል። በ2009 ዓ.ም. ደግሞ ኢንፍራስትራክቸር ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ተብሎ ተሰይሟል።

በ2013 ዓ.ም. በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 475/2020 መሠረት ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እንደ መንግስት የልማት ድርጅት ሲቋቋም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሚል ስያሜ ተሰጠው።

ተልዕኮ

  • በአገር አቀፍ ደረጃ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ ልማትን ማረጋገጥ
  • የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትን በከፊል አካባቢያዊነት በመተካት መቀነስ
  • የግንባታ ማሽነሪዎችንና ፕላንቶችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት እና ማሻሻል
  • ምርቶችን ለውጭ ገበያ ተደራሽ በማድረግ የኤክስፖርት ድርሻ ማሳደግ

ፋብሪካዎቹ

ፎርም ወርክ እና ስካፎልዲንግ
እርዝ ሙቪንግ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ
የምህንድስና መሣሪያዎች
የግንባታ ማሽነሪ አካላት

የምርት ዓይነቶች

  • ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ዶዘር፣ ሮለር፣ ሞተር ግሬደር
  • ክራሸር፣ ሳንድ ሜኪንግ እና ባቺንግ ፕላንቶች
  • ክሬን፣ ቴሌስኮፕ ፎርክሊፍት፣ ፎርም ወርክና ስካፎልዲንግ

የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የጥገናና የድህረ ሽያጭ አገልግሎት
  • የስልጠና አገልግሎት
  • የፕላንቶች ተከላ፣ ኮሚሽንግ እና ቴስቲንግ

ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ

የኢንዱስትሪው አመሰራረትና ታሪክ

ኢትዮጵያ ፕላሲቲክ ኢንዱስትሪ በ1960 ዓ.ም. በአምስት የስራ ፈጣሪዎች የተመሰረተ ሲሆን፤ በ1973 ዓ.ም. መከላከያ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪውን 55% ድርሻ በመያዝ እያስተዳደሩ ቀሪው 45% በአምስቱ መስራቾች እየተዳደረ ቆይቷል።

በ2004 ዓ.ም. ወደ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሲጠቃለል ስያሜው ኢትዮጵያ ፕላሲቲክ ኢንዱስትሪ በመባል ቀጥሏል፡፡ በ2013 ዓ.ም. በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ አዋጅ ቁጥር 475/2020 መሠረት ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እንደ መንግስት የልማት ድርጅት ሲቋቋም ኢንዱስትሪው በግሩፑ ስር እንደ አንድ ኢንዱስትሪ ተደርጓል።

ተልዕኮ

  • በፕላስቲክ ዘርፍ ተወዳዳሪ በመሆን ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን ማምረት
  • የውጭ ምንዛሪን በመተካት የሀገር ውስጥ ገበያን መደገፍ
  • ምርቶችን ዲዛይን ማድረግና ማሳደግ
  • አዲስ ቴክኖሎጂ በመቀናጀት ወደ ሀገር ማምጣት

ፋብሪካዎቹ

ፒ.ቪ.ሲ ፖይፕ
ኢንጀክሽንና ብሎ ሞልዲንግ
ፒ.ቪ.ሲ ፕሮፋይልና ሲሊንግ
ፒ.ፒ ባግ
ኮምፖዛይት

የምርት ዓይነቶች

  • ፒ.ቪ.ሲ ፖይፕ፣ ኤች.ዲ.ፒ ፖይፕ፣ ፒ.ፒ.አር ፖይፕ
  • ፖሊ ባግ፣ ፖሊ ሽት፣ ፖሊ ታቡላር
  • ፒ.ፒ.አር ፊቲንግ
  • ኮምፖክስ ሰብስቴንሽን ኢንክሎዥር

ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ

የኢንዱስትሪው አመሰራረትና ታሪክ

ፖወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በ2002 ዓ.ም በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር ተቋቁሞ ሲተዳደር ቆይቷል። በኋላም በሚንስቴሮች ምክር ቤት ደንብ አዋጅ ቁጥር 475/2020 መሠረት ተቋቋመው ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን፣ ፖወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግሩፑ ስራ እንደ አንድ ኢንዱስትሪ ተደርጎ ተቋቋመ።

ተልዕኮ

  • ለኤሌክትሪክ ፖወር ማመንጫ፣ ማስተላለፊያና ስርጭት ዘርፍ የሚያገለግሉ የኤሌክትሪክ ኢኩፕመንቶችና አክሰሰሪዎችን ዲዛይን ማድረግ
  • የኤሌክትሪክ ኢኩፕመንቶችን መገንባት፣ ማሻሻል (Upgrade) እና ለገበያ ማቅረብ
  • የፖወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪውን በእውቀትና በልምድ ማሳደግ
  • የፖወር ኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂን በሀገራችን ላይ ማስፋፋት

ፋብሪካዎቹ

ትራንስፎርመር ማምረቻ
ዋየርና ኬብል ማምረቻ
አውቶማቲክ ፖወር ፋክተር ኮሬክተርና ኮምፖክት ሰብስቴሽን
ሶላር ፓነል ማምረቻ
ሞተርና ጀነሬተር ማምረቻ

የምርት ዓይነቶች

ትራንስፎርመር፣ ዋየርና ኬብል፣ ፖወር ፋክተር ኮሬክተር፣ ኮምፖክት ሰብስቴሽን፣ ሶላር ፓነል/ሶላር ላንተር፣ ሞተርና ጀነሬተር፣ ተርባይን

የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • ሞተርና ጀነሬተር ጥገና
  • ትራንስፎርመር ቴስቲንግ
  • ዲስትሪቢውሽን ኮምፖክት ሰብስቴሽን ቴስቲንግ
  • ዋየርና ኬብል ምርት ቴስቲንግ

ፖወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገራችን የኃይል ልማት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው ተቋም ነው።

ሜታል ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ

የኢንዱስትሪው አመሰራረትና ታሪክ

የብረታብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር ካሉ ኢንዱስትሪዎች አንዱ ሲሆን፣ በ2002 ዓ.ም. በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር ተቋቋመ፡፡ ኢንዱስትሪው በመጀመሪያ አነስተኛና መካከለኛ የብረት ምርቶችን በማምረት ሲሰራ ቆይቶ፣ በ2003 ዓ.ም. ዋና መ/ቤቱን ወደ መከላከያ ሎጀስቲክስና ዳይሬክቶሬት ጋራዥ በመቀየር ሰባት ፋብሪካዎችን በመያዝ የተለያዩ የብረት መዋቅሮችና የኢንጂነሪንግ ስራዎችን እየከናወነ ቆይቷል። በ2013 ዓ/ም በሚንስቴሮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 475/2020 መሠረት ተቋማዊ ለውጥ ተደርጎ ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ በግሩፑ ስር በመቋቋም የብረት መዋቅሮችንና ኢንጂነሪንግ ምርቶችን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

  • የአምራችና የአገልግሎት ዘርፍ ዕድገትን የሚያፈጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ማበልፀግና ማስተላለፍ
  • ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ እና ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ልማት አስፈላጊ የሆኑ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት
  • የማምረቻና የአገልግሎት ፕላንቶችን ዲዛይን ማድረግ፣ መገንባትና ማሻሻል
  • የምናመርታቸውን ምርቶችና የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ለውጭ ገበያ ተደራሽ ማድረግ

ፋብሪካዎቹ

ስቲል ስትራክቸር
ኢኩፕመንት ማምረቻ
ጀልባ ማምረቻ
ታወር ክሬንና ሊፍተር

የሚመረቱ ምርቶች

  • ዌርሃውስ፣ ኢንዱስትሪያል ሼድ፣ ወርክሾፕ
  • ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፖወር ፕላንት
  • የውሃና የነዳጅ ታንከሮች
  • ድልድይ፣ ትሬለር፣ ስፖንዳ
  • የትራንስፖርት፣ የመዝናኛና የወታደራዊ ጀልባዎች
  • ስማርት የመንገድ መብራት ፖል
  • የሆስፒታል ስትሬቸር

አቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ

የኢንዱስትሪው አመሰራረትና ታሪክ

አቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ 1981 ዓ.ም. የመንግስት ተቋም ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም. በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስር ሲቋቋም አቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ ስያሜ ተሰጠው፡፡ በ2013 ዓ.ም. ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አካባቢ በሚንስቴሮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 475/2020 መሠረት ተቋማዊ ለውጥ ተደርጎ ተቋቋመ፡፡

ተልዕኮ

  • መሠረታዊ የብረት ውጤቶች ፍላጎት በማጥናት እና በመተንተን የካስቲንግ የሜተለርጂካል ቴክኖሎጂ ማሻሻል በማከናወን የሀገር በቀል ፈጠራ ባለቤት መሆን
  • የመሰረታዊ ቴክኖሎጂ እውቀቶች ትስስር በመፍጠር የሀገራችንን እድገት ከግብ ማድረስ
  • ከተጨባጭ የስራ እንቅስቃሴ የሚገኙ የስራ ልምዶችን በመጠቀም የሀገራችንን መሰረታዊ ብርታብረት ልማት ማፋጠን
  • ለሰው ሃይል ልማት ቅድሚያ በመስጠት ባለሙያዎችን ማብቃት

ፋብሪካዎቹ

የመለዋወጫ ፋብሪካ
የማቅለጫ ፋብሪካ
ዝቋላ እስቲል ፕሮሰሲንግ

የሚመረቱ ምርቶች

  • የማሽን መለዋወጫዎች
  • ሮለር
  • ስክራፐር ፕሌት
  • የተለያዩ ሳይዝ ያላቸው ፌሮዎች

የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • ጋልባናይዜሽን
  • ኤሌክትሮ ፕሮቲንግ
  • መካኒካል ቴስት
  • ኬሚካል ኮምፖዝሽን ቴስት
  • ሂት ትሪትመንት
  • ፕሌቲንግ
  • ሆት ዲፕ
  • ትሬኒንግ