የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የውሳኔ ሰጪ ማኔጅመንት የ2014 የበጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የውሳኔ ሰጪ ማኔጅመንት የ2014 የበጀት አመት የ9 ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
ባለፉት 9 ወራት በሪፎርም ስራዎች፣በኦፕሬሽን ስራዎች እና በመደበኛ የስራ አፈጻጸሞች ላይ የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች በፕላንና ፕሮግራም ክፍል ቀርበው ወይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
ግሩፑን ወደ ትርፋማነት ለማሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፣የገጠሙ ትግዳሮቶች በስፋት ተዳሰዋል፡፡

የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የግሩፑ ውጤታማነት ላይ ጫና እያሳሩ የሚገኙ ጉዳዮችን ለመፍታት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በጆይንት ቬንቸር እና በሌሎች አማራጮች ከተለያዩ የውጭ ሃገራት ኩባንያዎች ጋር ለመስራት ተከታታይ ምክክሮችና የመግባቢያ ስምምነቶች እየተፈረሙ በመሆናቸው እነዚህን ከዳር ለማድረስ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ይህም ወደ ተቋሙ ቴክኖሎጂ፣ ፋይናንስና የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማምጣት የሚረዳ ነው፡፡
ተቋሙን የውጭ ምንዛሪ ፈላጊ ሳይሆን የውጭ ምንዛሪ የሚያስገባ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግም ተነስቷል፡፡እንደ ሶማሊ ላንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ጅቡቲና ኬንያ ያሉ የጎረቤት ሃገራትን ታሳቢ ያደረገ ስራ ለመስራት እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ናቸው ብለዋል፡፡
በመሆኑም የምርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሰርተፊኬሽን እንዲረጋገጥ በቀሪ ወራት ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
የተቋሙን ገጽታ ለመቀየር እንዲቻል ሰፊ የሆነ የሪ ብራንዲንግ ስራ እየተሰራ ሲሆን ይህንን በአጭር ጊዜ ይፋ በማድረግ የገጽታ ግንባታ ስራ ላይ ትልቅ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡
የቀጣይ የበጀት አመት እቅድ ዝግጅት ላይ ትኩረት በማድረግና ሊሳካ የሚችል ተጨባጭ መነሻ ያለው እቅድ ለማዘጋጀት ከወዲሁ ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ኢንዱስትሪዎች ከዋና ስራ አስፈጻሚ ጋር በመፈራረም ወደ ተግባር ይገባሉ ተብሏል፡፡
አጠቃላይ ስራውን ወደ ተግባር ለመቀየር እገዛ የሚያደርግ ቲም በመቋቋም ላይ መሆኑን እና ከዚህ ቲም ጋር ተቀናጅቶ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ ነው የተመላከተው፡፡
እነዚህ ተግባራቶች ላይ ርብርብ በማድረግ ተቋሙን ወደ ትርፋማነት ለማሸጋገር እንደሚሰራ ተመላክቷል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *