የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች በግሩፑ ስር የሚገኙትን ኢንዱስትሪዎች መጎብኘት ጀመሩ፡፡
በዛሬው እለት ማለትም ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪንና በፓወር ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘውን የሞጆ ዋየርና ኬብል ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የሃገሪቱን ግብርና በማዘመን ረገድ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ትልቅ ሃላፊነት የተጣለበት ተቋም መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይህንን ሚናውን በይበልጥ መወጣት እንዲችል በምርምርና ልማት ስራ መደገፍ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ከፍተኛ አመራሩ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ የታዩ ተስፋዎችን ለማስቀጠልና ማነቆዎቹን ለመፍታት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ኢንዱስትሪውን በይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ሰራተኛውን ባለቤት በማድረግና በማነቃቃት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
የሞጆ ዋየርና ኬብል ፋብሪካም ይበልጥ እንዲዘምንና ለሃገሪቱ የሃይል ዘርፍ የሚያበረክተው አስተዋጽ ማደግ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተካሂዷል፡፡
በጉብኝቱ ላይ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች፣አማካሪዎችና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡
የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን ትራክተሮች፣ማረሻና መከስከሻ፣ የውሃ መርጫ ፓምፖችን በማምረት ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይ የሞጆ ዋየርና ኬብል ማምረቻ የተለያየ መጠን ያላቸውን የኤሌክትሪክ ገመዶችን በማማረት ለኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎትና ለተለያዩ ደንበኞች የሚያቀርብ ፋብሪካ ነው፡፡



