የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮች ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎበኙ፡፡

የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው እለት ማለትም ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል፡፡
በኢንዱስትሪው ስር የሚገኙ ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎችን የሚያመርቱ የተለያዩ ፋብሪካዎችን ጨምሮ ሌሎችም የስራ ክፍሎች ተጎብኝተዋል፡፡
ኢንዱስትሪው የአዲስ አበባን ጨምሮ የተለያዩ የሃገሪቱን ክፍሎች የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት ተልእኮውን በአግባቡ እንዲወጣ የውስጥ አቅምን አሟጦ በመጠቀም መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ለኢንዱስትሪው ውጤታማነት የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮች ያልተቆጠበ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አረጋግጠዋል፡፡
ኢንዱስትሪው አሁን ከያዛቸው ምርቶች በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ወደ ማምረት የሚገባበት አማራጮች መታየት እንዳለባቸው የጠቆሙ ሲሆን ይህም በየጊዜው እየጨመረ ካለው የነዳጅ ዋጋ አንጻር ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢንዱስትሪውን ወቅታዊ የውጭ ምንዛሪ ችግር ለመቅረፍ በሰፕላየር ክሬዲት አሰራር አማራጮች እየተመቻቹ ይገኛል፡፡
በጉብኝቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች፣አማካሪዎችና የማኔጅመንት አባላት እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናቶችም በሌሎች ኢንዱስትሪዎች ይቀጥላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *