የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኦፕሬሽን ዘርፍ ከኢንዱስትሪዎች ኦፕሬሽንና ተጠሪ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኦፕሬሽን ዘርፍ ከዘጠኙ ኢንዱስትሪዎች ኦፕሬሽንና ተጠሪ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ።የቀጣይ ወራቶች እቅድና የክትትል እና ድጋፍ ስራ በትኩረት ተዳሰዋል ። በውይይቱ የመረጃ እና የሪፖርት ቅብብሎሽ ስርአቱ ወጥነት የጎደለው መሆኑን በመገምገም ማሻሻያ ተደርጎበታል ።የክትትልና ድጋፍ ስርአቱን ወጥነት እንዲኖረው በማድረግ በምርት ጥራት፣ በማቅረቢያ ዋጋና ጊዜ ላይ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ያስችላል።በሌላ በኩል ያለፈው 6 ወራት አፈፃፀም እንደ መነሻ ተወስዶ የቀጣይ 5 ወራት ዕቅድ ክለሣ ተደርጓል፡፡ በ6 ወራቱ አፈፃፀም የነበረውን ጠንካራ ጐን በመያዝ ድክመት ላይ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ውይይቱን የመሩት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሐመድ ጀማል ገልፀዋል፡፡ ያለንን አቅምና ምቹ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት አቅደን ስንሰራ ውጤታማ እንሆናለን ያሉት ኃላፊው ለዚህም ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *