በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የካይዘን ሽልማት አሸናፊ ሆነ።
ኢንዱስትሪው ከአምራች ሁለተኛ ደረጃ በማግኘት ነው ተሸላሚ የሆነው።
የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርአቱ በትላንትናው እለት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣ የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ታደሰ እና የኢንዱስትሪ ሀላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
8ኛው አመታዊ የካይዘን ሽልማት የተካሄደው በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ነው።
በእውቅና ስነ ስርአቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የኢንዱስትሪ፣ ማእድንና የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣የ አይ.ኤል.ኦ የምስራቅ አፍሪካ ሀላፊ፣ የጃይካ JICA ካንትሪ ዳይሬክተር ተገኝተዋል።
‘ካይዘን ኢትዮጵያ ታምርት’ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የእውቅና መድረክ ላይ 19 ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅና ተሰቷቸዋል።
በግለሰብ፣በግል፣በቡድን፣በአገልግሎት እና በተቋማት አምራች ዘርፍ ነው እውቅና የተሰጠው።