የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ውሳኔ ሰጪ ማኔጅመንት በግሩፑ የ2015 አ.ም የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ውሳኔ ሰጪ ማኔጅመንት በግሩፑ የ2015 አ.ም የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ፡፡
በምርት አፈጻጸም፣በኦፕሬሽን ስራዎች፣በትርፍና በገቢ አፈጻጸም፣ አስተዳደራዊ ወጪዎችን በመቀነስ እንዲሁም በገበያ እና በሪፎርም ስራዎች ላይ ያለው አፈጻጸም በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በዚህም ጠንካራ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች ጥንካሬያቸውን እንዲያስቀጥሉና ክፍተት ያለባቸው ኢንዱስትሪዎች ክፍተታቸውን እንዲያስተካክሉ ተገምግሟል፡፡
በውይይቱ ወቅት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ኢንዱስትሪዎች በተለይም የእሴት ጭማሪ ስራዎች ላይ በማተኮር መስራት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡
ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የሚደረጉ ስምምነቶችም ኢንዱስትሪዎቹን ትክክለኛ የአምራች ቁመና ላይ የሚያሰልፉ መሆን ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የሃገሪቱን ቁልፍ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ምርቶች ላይ አትኩረው እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
የበጀት አመቱ ቀሪ ወራቶች ላይ ያልተሳኩ ግቦች ላይ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
የየኢንዱስትሪው ማኔጅመንት የተመዘገቡትን አፈጻጸሞች ከሰራተኛው ጋር የጋራ በማድረግ መንቀሳቀስ እንዳለበትም ተመላክቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *