በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የምርምርና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ስራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ።
ውይይቱ በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለ የስራ ትስስር ለመፍጠር፣የዲዛይንና ልማት ስራዎችን ለማጠናከር እንዲሁም በዘጠኙም ኢንዱስትሪዎች ያሉ የምርት ክምችቶች ወደ ጥቅም መቀየር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
የግሩፑ ምርምርና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሠረት ደስታ ገበያ ለመፍጠር፣ ምርታማነትን ለመጨመር፣ ኢንዱስትሪዎችን በተሻለ ጥራት ተወዳዳሪ ለማድረግ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቀነስ በትስስር መስራት እንደሚገባ ገልፀው፤ በቀጣይ ሊተገበሩ የሚገቡ ስራዎች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የኢንዱስትሪዎች የገበያ ትስስርን ማሳደግ እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን ግሩፑን ትርፋማ ለማድረግ በክምችት የሚገኙ ምርቶችን በመለየት፣ ዋጋ በማውጣትና ደንበኞችን በመለየት ለሽያጭ ማቅረብ ላይ በትኩረት ለመስራት ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በውይይቱ የዘጠኙ ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጆች፣የኢንዱስትሪዎች ዲዛይንና ልማት ሀላፊዎች እንዲሁም የሽያጭ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።