በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማዕድንና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራ ልዑካን ቡድን በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የመስክ ምልከታ አካሄደ።

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማዕድንና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተመራ ልዑካን ቡድን በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የመስክ ምልከታ አካሄደ።
ከማእድንና ኢንዱስትሪ  በተጨማሪ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ጉዳይ ፣ጤናና ማህበራዊ ጉዳይ፣የመንግስት ልማት ድርጅትና የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎችን ጨምሮ የካይዘን የልህቀት ማዕከል አስፈፃሚዎች በኢንዱስትሪው ተዘዋውረው ጉብኝት አካሂደዋል።
ኢንዱስትሪው እያካሄደ ያለዉ የምርት እንቅስቃሴ እና የካይዘን አፈፃፀሙ ተጎብኝቷል ።
ኢንዱስትሪው በግቢ፣በዎርክሾፕ እንዲሁም በቢሮ ካይዘን ባደረገው አፈፃፀም ከአምራች ዘርፍ የአፍሪካ ካይዘን ሽልማት ማግኘቱ ይታወቃል።
በእለቱ በተደረገ ውይይት የማእድንና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር አማረች ባኮሎ ይህ ኢንዱስትሪ ሀገራችን በእርሻ ዘርፍ ያለባትን ክፍተት ከመሙላቱም አልፎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን የሚጠይቁ ምርቶችን በሀገር መተካት የሚያስችል ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይም ከዩንቨርስቲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ያሉትን ክፍተቶች መሙላት እንደሚገባ ገልፀዋል።ኢንዱስትሪው የካይዘን ፍልስፍናን በተግባር ማሳየቱ ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ የሚሆን ተግባር እንደሆነም አንስተዋል።
የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ታደሰ ለኢንዱስትሪው ለውጥ በቅድሚያ ችግሮቻቸውን በባለቤትነት መቀበላቸው ወደ መፍትሔው ለመድረስ እንዳገዛቸው ገልፀው በቀጣይም ኢንዱስትሪውን በኢትዮጵያ ቀዳሚ ትራክተር ፋብሪካ ለማድረግና ምርቶችን ለውጭ ሀገራት ለማቅረብ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በቀጣይም ደንበኞች ባሉበት ስፍራ የድህረ ሽያጭ አገልግሎት ለመስጠት እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነም ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *