የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንትና የመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ ፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንትና የመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ ፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር  ዮሀንስ አያሌው ፣ከመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር አቶ ገረመው ቀኖ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪን  ጎብኝተዋል ፡፡
በእለቱም በአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በቀጣይ ከባንኩ ጋር በትስስር ለመስራት ብሎም የጋራ የመግባብያ ስምምነት በመፈራረም መስራት  የሚቻልበት ሁኔታ ላይ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣ የግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚዎች በተገኙበት ሰፊ ምክክር ተደርጓል፡፡
የውጭ ምንዛሬን በመቀነስ ለሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ማሽነሪዎችን በቀጥተኛ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡
ባንኩ ከኢንዱስትሪው ከአምስት መቶ እስከ አንድ ሺህ ትራክተሮችን በቀጥታ ግዢ በመፈፀም ለከፍተኛ፣ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንቨስተሮች እንዲሁም ለአርሶ አደሮች ለማስጠት እንዳቀደ የተገለፀ ሲሆን ይህም ሀገሪቱ በዘርፉ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ፋይዳው የላቀ ነው።
በተመሳሳይ በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በተካሄደው ውይይት ኢንዱስትሪው ያለበት የጥሬ እቃ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢንዱስትሪው ጋር እንደሚሰራ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *