በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ  የህጻናት ማቆያ ማእከል ተጠናቆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

መጋቢት 2/2016 ዓ.ም (ኢ.ኢ.ግ) የዘንድሮው አለም አቀፉን  የሴቶች ቀን በኢንዱስትሪው ሲከበር የህጻናት ማእከሉ ተጠናቆ ተመርቋል፡፡
ማእከሉ ለህፃናት እንክብካቤ በሚያመች መልኩ በሰራተኞች ተሳትፎ የማስፋፊያ ግንባታ ተከናውኖለታል፡፡
ማእከሉ በ500 ስኩዌር ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን በዕድሜ  ከ6 ወር እስከ 4 ዓመት  የሚደርሱ 80 ህፃናትን ተቀብሎ እንክብካቤ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ማእከሉ  እስከ 200 ህፃናትን የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን ለ14 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡
የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ ምርትና ማእከሉ ምርታማትን ለማስቀጠል፣ ሰላማዊና ምቹ የስራ ቦታን ለመፍጠር ፋይዳው የጎላ መሆኑን በመጥቀስ ለማእከሉ መጠናቀቅ የበኩላቸውን የተወጡትን ሰራተኞች አመስግነዋል፡፡
የግሩፑ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አገልግሎት ኃላፊ ወ/ት በረከት አሰፋ  በግሩፑ እና በስሩ ባሉት ኢንዱስትሪዎች ላይ ለሴቶች ልዩ ትኩረት በመስጠቱ የመሪነት ሚናቸውን  እንዲወጡ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ ሴቶች የተጎናጸፉትን ድል ለማስቀጠል ወደኋላ የሚጎትትታቸውን በጎን በመተው ራሳቸውን በማብቃት ሁልግዜ ዝግጁ መሆን  እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 
በፕሮግራሙ ላይ ድጋፍ ለሚሹ የቀን ሰራተኞች የዘይትና የምግብ  ድጋፍ የተበረከተ ሲሆን ማእከሉ እንዲጠናቀቅ  በጉልበትና በሙያቸው ለሰሩ  ሰራተኞች እውቅና ተሰቷቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *