ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋም  የሚያስችል 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ ፡፡

ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም (ኢኢግ) ግሩፑ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ዜጎችን ለማቋቋም የሚያስችል ሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበርክቷል፡፡
ግሩፑ ድጋፉን ያበረከተው የመንግስት ልማት ድርጅት ይዞታና አስተዳደር  ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጋር ባዘጋጀው የድጋፍ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምክትል ዋ/ስ/አስፈፃሚና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሃላላ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙ ሲሆን እንደ ግሩፕ ጉዳት ለደረሰባቸው የማሕበረሰብ አካላት  የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን  በመግለፅ ግሩፑ ለተጎጂዎች ያዘጋጀውን ድጋፍ አበርክቷል፡፡  በማስቀጠልም የማህበረሰቡን ዘላቂ ድጋፍ ለማድረግ በአብሮነት በሚሰሩ ስራዎች ውስጥ ግሩፑ ማሳየት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል  አስገንዝበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *