የመንግስት ሰራተኞችን ትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሃምሳ ሚድ ፍሎር ባሶች ተመርተው ለተጠቃሚው እንዲደርሱ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ተገጣጥመው ለፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ድርጅት ከዚህ ቀደም የቀረቡት የዩቶንግ አውቶብሶች የትራንስፖርት እጥረቱን ለመቅረፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡
ይህንን ልምድ በማስቀጠል በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ አውቶብሶችን ለተጠቃሚ ለማድረስ እንደሚገባ በውይይቱ የተገኙት የስራ ሃላፊዎች አንስተዋል፡፡
በተለያዩ አማራጮች አውቶብሶቹን ለማቅረብ ምክክር እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ቴክኒካዊ እና የስፔሲፊኬሽን ግምገማ ጉዳዮችን በፍጥነት በመጨረስ ወደ ትግበራ ምእራፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይገባል ተብሏል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የማኔጅመንት አባላት፣በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ጂግሶ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ከዩቶንግ ኩባንያ ሚስተር ሉቃስ እና የስራ ባልደረቦቻቸው ተገኝተዋል፡፡
የስራ ሃላፊዎቹ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪን የባስ ማመረቻ ዎርክ ሾፕን እና በቅርቡ በኢንዱስትሪው የተገጣጠሙትን ኤን 7 ፒክ አፕ ተሸከርካሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡











