ኢኢግ(ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና ሻንዶግ ሻንቱኢ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ምርት ዘርፍ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡
የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ግብአቶችን ማቅረብን ያካተተው ስምምነቱ የቴክኖሎጂ ሽግግርም ትኩረት ተደርጎበታል፡፡
በቀጣይ ማሽነሪዎቹን በሀገር ውስጥ ማምረት እንዲቻልም ታሳቢ ተደርጓል፡፡
በግሩፑ ስር ከሚገኙት ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪን ማዘመን የስምምነቱ ዋነኛ አላማ ነው፡፡






