ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ (EEG) በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 475/2013 መሠረት በመስከረም 2013 ዓ.ም እንደ የመንግስት ልማት ድርጅት እንደገና የተቋቋመ አምራች ተቋም ነው።
እንደገና የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን በመገንባት በሀገሪቱ የኢንዱስትሪ መሠረት ያለው ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ ሚና መጫወት እንዲችል ነው።
በመሆኑም ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በግብርና ማሽነሪዎች፣ ኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ የኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ፣ ማሰራጫና መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች፣ የብረታ ብረት ውጤቶች እንዲሁም የፕላስቲክና ኮምፖዛይት ምርቶች ዘርፍ የተሰማራ አምራች ተቋም ነው።
ግሩፑ በሀገራዊና ዓለማቀፋዊ የነፃ ገበያ ህጎች የሚመራ ሲሆን፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ አምራቾች ጋር በመተባበር በጋራ የሚሠራ ተቋም ነው።
በአሁኑ ጊዜ በአገራችን የቴክኖሎጂ እድገት ጉልህ ድርሻ ያላቸው የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርቱ፣ የራሳቸው የማምረቻ ፋሲሊቲዎች ያላቸው ሰባት ኢንዱስትሪዎችን ያቀፈ ተቋም ነው።
በ2022 ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕን የሚተማመኑበት አምራችና የዘርፉ የልሕቀት ምህዋር ማድረግ
ኢትዩ-ኢንጂነሪንግ ግሩች የፌዴራል መንግስትን ስተራቴጂ እቅድ መነሻ በማድረግ ያቅዳል ግሩፑ ፖርትነር ሽፕ ለእድገቱ ቁልፍ ነው ብሎ ያምናል የኛ የሥራ አጋሮች ደንበኞቻችን፣ ሰብኮንትራክተሮች እና አቅራቢዋቻችን ሲሆኑ ቀጣይነት ላለው እድገት እና ለጋራ ስኬት ወሳኝ ነው፡፡