Ethio Engineering Group

ፖሊሲ

የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፖሊሲ

  1. የአምራች ኢንዳስትሪውን እና የአገልግሎት ዘርፉን እድገት የሚያፋጥኑ ቴክኖሎጂዎችን ማበልፀግና ማስተላለፍ፣
  2. ከፍተኛ የገበያ ክፍተት ያስከተሉ፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ፣ እና ለሀገራዊ የኢኮኖሚ ልማት ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ እያመረቱ መተካት፣
  3. የማምረቻና አገልግሎት መስጫ ፕላንቶችን ዲዛይን ማድረግ፣ ማምረት፣ መገንባት፣ ማደስ፣ እና ማሻሻል፣
  4. የምናመርታቸውን ምርቶችና የምንሰጣቸውን አገልግሎቶችን ለውጭ ገበያ ተደራሽ በማድረግ የሀገሪቱን ኤክስፖርት ድርሻ ማሳደግ።

ከላይ የተጠቀሱትን ተልዕኮዎች ለማሳካት የግሩፑ ከፍተኛ አመራር የ ISO 9001:2015 የጥራስ ስራ አመራር መስፈርትን መሰረት በማድረግ የግሩፑ ምርቶች እና አገልግሎቶች በሙሉ ጥራታቸውን በመጠበቅ በተፈላጊ ጊዜ ተደራሽ እንዲሆኑ በተመጣጣኝና ተወዳዳሪ ዋጋ ለደንበኞች ማቅረብ በቁርጠኝነት ይሰራል።

ቀጣይነት ያለው መሻሻል በመፍጠር የጥራት አስተዳደር ስርዓት ለመገንባትና ለመተግበር ይተጋለጣል።

የግሩፑን አውድ በማስገባት የጥራት ስርዓቱን ከስትራቴጂክ እና ኦፕሬሽናል ዓላማዎች ጋር በማጣጣም ቀልጣፋ፣ ውጤታማ፣ አስተማማኝ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለማቅረብ ይሰራል።

ይህን የጥራት ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ የሚከተሉት ይተገበራሉ፦

  • በምናመርታቸው ምርቶች እና በምንሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ቀጣይነት ያለው ማሻሻል እና የጥራት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት፣
  • የሰው ኃይል፣ የቴክኖሎጂ፣ የችግር ፈቺነት እና የፋይናንስ አቅም መገንባት፣
  • የደንበኛ ፍላጎትን የሚያሟሉ ምርቶች መስጠትና ማረጋገጥ፣
  • በአጋርነት መርህ የተመሰረተ የኢንዱስትሪ ትስስር መፍጠር፣
  • አዳዲስ ምርቶችን በማምረት አዳዲስ ደንበኞች መሳብ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣
  • ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከጥራት አስተዳደር ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማኔጅመንት የሚያበረታታ።