የግሩፑ ውሳኔ ሰጪ ማኔጅመንት አባላት በእቅዱ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ግሩፑ በ2017 አ.ም ካመረተው ምርት ላይ የ37 በመቶ ጭማሪ ምርት ማምረት የሚያስችለውን አቅድ አዘጋጅቷል፡፡
የግሩፑ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በዋናነት ያለፉትን ዓመታት አፈጻጸም ግምገማ መነሻ በማድረግ ፣ግሩፑ ያልተጠቀማቸውን አቅሞች በተሻለ ለመጠቀም የታቀደ ነው፡፡
በ2018 የበጀት አመት የግብርና ማሽነሪዎችን፤ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችንና መሳሪያዎችን፤ የሃይል መሰረተ ልማት ዘርፍ ምርቶችን፤ የብረታ ብረት ዘርፍ ምርቶችን ፣መለዋወጫዎች፤ የብረት ውቅር ሥራዎች፤ የፋብሪካ አካላት እንዲሁም የፕላስቲክ ውጤቶችን በማምረት ለገበያ ለማቅረብ ታቅዷል፡፡
ከምርትና አገልግሎት ሽያጭ ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ በላይ ለማግኘት ታቅዷል፡፡ ከኦፕሬሽን ከሚገኝ ገቢ በተጨማሪ ከሌሎች የተለያዩ ምንጮች 29.87 ሚሊየን ብር ገቢ እንዲሁም ትርፍ ከታክስ በፊት 299.74 ሚሊየን ብር ለማግኘት ታቅዷል፡፡
ለኢንዱስትሪዎች ቁልፍ ማነቆ የሆነውን የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የግብዓት ማሟላት ሥራ የተለያዩ አማራጮችን በመፈተሽ ለመጠቀም ጥረት የሚደረግ ሲሆን ከኦሪጅናል አምራች ኩባኒያዎች ጋር የረጅም ጊዜ ውል በማሰር ወደ ተግባር ለመግባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡
ግሩፑ እቅዱን ለማሳካት የፋይናንሻል ሪፎርም ሥራዎች ላይ በትኩረት መስራት፤የአሰራርና አደረጃጀት ማሻሻያ፤አሰራሩን በኢ አር ፒ መደገፍ፤ካይዘንን መተግበር፣የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማሳካት ፤የሙያ ስታንዳርድ ሰርቲፊኬሽን ሥራዎችን ማከናወን ላይ በትኩረት ይሰራል፡፡የምርት፤ የተቋማት አሰራርና የፋሲሊቲ ስታንዳርድ ሰርቲፊኬሽን ሥራዎች ላይም በስፋት ይሰራል፡፡
በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ወጪያቸው 523.6 ሚሊየን ብር የሚገመት 5 ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ደብረማርቆስ ታወር ክሬንና ሊፍተር ፋብሪካን የኢሬክሽን ፣ቴስት እና ኮሚሽን ስራ ማከናወን፤ኮንስትራክሽን ማ/ማ/ኢንዱስትሪ/ደብረ ብርሃን ዎርክሾፕ ግንባታን የማሽኒግ እና አሴምብሊንግ ወርክሾፕ ግንባታ ማከናወን፤ደብረብርሃን ቤሪንግ ፋብሪካ ፕሮጀክትን የማጠናቀቂያ እና የማሽን ኢንስታሌሽን፣ እና ፍተሻ ስራ መስራት፤ዝቋላ ስቲል ሮሊንግ ፋብሪካ ፕሮጀክት የሲቪል ስራዎች እና የሪቫምፒንግ ስራ ለማከናወን ታቅዷል፡፡እንዲሁም የምርምርና ልማት ወርክሾፕ ግንባታ ስራ በቀጣዩ የበጀት አመት ይከናወናል፡፡
የኮርፖሬት ገቨርናንስ ሥራዎች ላይም በማተኮር በውጭ ኦዲት ስራ የግሩፑን ሂሳብ የውጭ ኦዲት ከማጠናቀቅ አንጻር ቀደም ሲል ሲሸጋገሩ የመጡ የባክ ሎግ ሥራዎች እንዲጓተት ያደረጉት በመሆኑ ይህንን ችግር ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ለመስጠት በተደረገው ጥረት እስከ 2017 ዓ/ም የ2013 ሂሳብ እና የ2014 ሂሳብ ለኦዲት ቦርድ ኮርፖሬሽን ቀርቦ ምርመራ የተጠናቀቀ ሲሆን የ2015 እና የ2016 ሂሳብ ምርመራ እንዲደረግ ለኮርፖሬሽኑ ቀርቧል፡፡
የውስጥ ኦዲት ግኝትን በ2017 በአማካይ ከነበረበት 75% ወደ 80% ማድረስ የሚያስችል እቅድ ተዘጋጅቷል።
የግሩፑ ማኔጅመንት አበላት እቅዱ መሳካት በሚችልበት ሁኔታ ላይ ጥልቅ ውይይት አካሂደዋል፡፡


