በመርሀ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ በነባር አመራሮች የተጀመሩ ስራዎችን በማስቀጠል እና ከግሩፑ አመራርና ሰራተኞች ጋር መልካም የስራ ግንኙነት በመፍጠር ግሩፑን ስኬታማ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው በግሩፑ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችንና ቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በግሩፑ እየተካሄዱ የሚገኙትን የስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት፣የመመሪያዎች ክለሳ፣ተቋማዊ አደረጃጀት፣የኦዲት ሰራዎችን በማጠናቀቅ ግሩፑን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ያልተቆራረጠ ግብአት የሚገኝበትን መንገድ በማመቻት ቀጣይነት ያለው ምርት እንዲኖር ይሰራልም ብለዋል፡፡
ም/ዋና ስራ አስፈፃሚዎችን ወክለው ንግግር ያደረጉት ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ሁላችንም በቡድን መንፈስ ተባብረን በመስራት ለተቋሙ አሻራችንን እናሳርፋለን ብለዋል፡፡
ግሩፑን በም/ዋና ስራ አስፈፃሚነትና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሳሙኤል ሃላላ በግሩፑ ላይ በነበራቸው ቆይታ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች በጋራ በመሆን ከካይዘን ስራዎች ጋር፣ ከንብረት አያያዝ ስራዎች የተሰሩ መልካም ጅምሮች እንዲቀጥሉና ለአዲስ አመራሮች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡
የግሩፑ ቦርድ አባል አቶ ከበደ ገለታ ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ የተመደቡ አመራሮች ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ ለተቋሙ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡ ተቋሙን ከሌሎች የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር ተወዳዳሪ ለማድረግ በትጋት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
የግሩፑ የስራ አመራር ቦርድ አባል ዶ/ር ዲንሰፋ መንሱር (ተ/ፕሮፌሰር) ለሃላፊዎቹ እውቅና አበርክተዋል፡፡