ሃምሌ 18/2017 ዓ.ም (ጋምቤላ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በጋምቤላ ክልል የክረምት በጎ አድራጎት ስራዎችን አካሄደ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ እና የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ እና ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በበጎ አድራጎት መርሃ ግብሩ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
ሶስት አቅመ ደካማ ቤቶች እድሳት ለማከናወን የማስጀመሪያ ስነ ስርአት ተካሂዷል፡፡
በተጨማሪም ለአንድ መቶ ተማሪዎች ቦርሳን ጨምሮ ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ስጦታ ተበርክቷል፡፡
የክልሉ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በሃገር አቀፍ በተያዘው የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብር ላይ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ወደ ጋምቤላ በመምጣቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ ግሩፑ አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ ያደረገው ጥረት የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ በበኩላቸው ክልሉ ላደረገላቸው አቀባበል አመሰግነው በቀጣይ በተለያዩ ዘርፎች ከክልሉ ልማት ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል፡፡
የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ሳይመን ሙን እና የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ የቤት እድሳት ፕሮግራሙን አስጀምረዋል፤ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍንም ከአምስት ቀበሌ ለተውጣጡ ተማሪዎች አበርክተዋል፡፡
በጋምቤላ ከተማ በተካሄደው የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር በግሩፑ ስር የሚገኙት የፓወር ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *