ሀምሌ 24 2017ዓ/ም (ኢኢግ) የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አመራርና ሰራተኞች 700 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተሳተፉ።

የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ በፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ሞጆ ዋየርና ኬብል ማምረቻ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ተከናውኗል።
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞች መንከባከብም እንደሚገባ ተናግረዋል።
የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያደኑ ትርፌሳ በበኩላቸው የእንኳን ደህና መጣቹ መልዕክት አስተላልፈው በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች መተከላቸው የግቢው ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚሆን ገልፀዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይም ዋናው መ/ቤትን ጨምሮ የፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፣ አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪና ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ አመራርና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
የግሩፑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፋብሪካውን ጎብኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *