ግሩፑ በስድስት ወራት በምርት፣ በሽያጭ፣ በገቢና በትርፍ እንዲሁም በተሰብሳቢ ያስመዘገበው ውጤት ካለፉት አመታት አንጻር የተሻሻለ መሆኑ በቦርዱ ተገምግሟል፡፡
ግሩፑ በተሰማራበት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አዳዲስ ምርቶችን በማምረት ለገበያ ለማቅረብ እየሰራ ስለመሆኑም ቀርቧል፡፡
ተቋሙ ያሉበትን የህግ ጉዳዮች በድርድር መፍታቱ እና ያልተወራረዱ የውጭ ምንዛሪን ማወራረዱ በቦርዱ በጥንካሬ የተገመገሙ ናቸው፡፡
የኦዲት ስራው በተመሳሳይ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እና ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ያላለቁት ስራዎች እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ግሩፑ ካለው አቅም አንጻር ብዙ ጥረት በማድረግ ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚያስፈልገው ተገምግሟል፡፡
የፋይናንስ ፍሰትን ማረጋገጥ፤ የሰው ሃይልንና የማሽን አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሳደግ፤ ጠንካራ የስራ ባህልን በመገንባት ግሩፑን የበለጠ ተወዳዳሪ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የደንበኛ እርካታን ማሳደግ፣ የቢዝነስና የገበያ ስራን ማሳደግ በቀጣይ በትኩረት እንዲሰሩ የሚጠበቁ ተግባራት መሆናቸው ተለይቷል፡፡
የስራ አመራር ቦርዱ ከስራ አፈጻጸም ውይይት በተጨማሪ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተከልሰው የቀረቡ ስምንት መመሪያዎችን አጽድቋል፡፡
በተያዘው የበጀት አመት ጸድቀው በስራ ላይ ከሚገኙት አምስት መመሪዎች ጋር በአጠቃላይ በበጀት አመቱ አስራ ሶስት መመሪያዎች ጸድቀዋል፡፡












