የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከውሳኔ ሰጪ ማኔጅመንት ጋር የመጀመሪያ ውይይታቸውን አካሄዱ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከውሳኔ ሰጪ ማኔጅመንት ጋር የመጀመሪያ ውይይታቸውን አካሄዱ፡፡
በውይይቱ ላይ የሃብት አሰተዳደር ዘርፍ ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ገ/ማርያምና የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ ዘርፋቸው የሚገኝበትን ደረጃ ለዋና ስራ አስፈጻሚው አብራርተዋል፡፡
ሁለቱም ዘርፎች የሚገኙበትን ደረጃ፣ጥንካሬና ድክመቶች እንዲሁም ወደፊት ሊወሰዱ የሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ግሩፑ የጀመራቸውን የለውጥ ስራዎች በማስቀጠል ወደ ትክክለኛ የቢዝነስ ተቋም ለማሸጋገር እንደሚሰሩና ለዚህም ያላቸውን እምነትና ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
ከተለመደው የቢሮክራሲ አካሄድ መውጣትና የንግድ ሰራ ባህሪን ተላብሶ መስራት እንደሚገባ በመጥቀስ፡፡
የግሩፑን የሪብራንዲንግ ስራ በማጠናከር የገጽታ ግንባታ ላይ ብዙ መስራት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
ለዚህም ደግሞ የቡድን ስራ እና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሳሪዎች ተብለዋል፡፡
ተቋሙ ያለውን አቅም በአግባቡ በመፈተሸ የሚችለውንና ውጤታማ የሚሆንበት ስራ ላይ ብቻ እንዲሰማራ ይደረጋል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ለዚህ ውጤታማት ከማኔጅመንቱ ጋር በመሆን እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
ከአለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በተለያዩ መንገዶች በመስራትም ግሩፑን ውጤታማ ለማድረግ ይሰራልም ተብሏል፡
የግሩፑ ትኩረት ጥራት ላይ መሆኑን ያስገነዘቡት አምባሳደር ምስጋኑ በዚህም ሃገር የምትኮራበትን ምርት ማምረት እንደሚጠይቅ አንስተዋል፡፡
በቀጣይ የጉብኝትና የምክክር ፕሮግራሞችን ከኢንዱስትሪ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር እንደሚያካሄዱም አስታውቀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *