ለግሩፑ የቀድሞ ስራ አስፈጻሚ ሽኝትና ለአዲሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ የአቀባበል ስነ ስርአት ተከናወነ

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የጀመረውን የሪፎርም ጉዞ ከዳር በማድረስ ምርታማነቱን ማረጋገጥ እንዳለበት የግሩፑ የቦርድ ሰብሳቢና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም በላይ ተናገሩ፡፡
ዶክተር አብረሃም ይህን የተናገሩት የግሩፑ የቀድሞ ስራ አስፈጻሚ በተሸኙበትና ለአዲሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ በተደረገ የአቀባበል ስነ ስርአት ላይ ነው፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ዶክተር አብረሃም ግሩፑ የተጀመሩትን የሪፎርም ስራዎች ማጠናከር አለበት ብለዋል፡፡
ጥራት ያላቸውን ምርቶች በማምረት ወደ ትርፋማነት የሚያደረገውን ጉዞ ማፋጠን እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ግሩፑን እንዲመሩ የተሾሙት አዲሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው የተጀመሩትን የለውጥ ስራዎች በማስቀጠል ግሩፑ ለሃገር የሚጠቅም ተቋም ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በገበያ አስተሳሰብ የሚመራ እና ጥራትን መለያው ያደረገ ተቋም እንገነባለን ብለዋል፡፡
ሽኝት የተደረገላቸው የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ህይወት ሞሲሳ በበኩላቸው በሪፎርም ሂደት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውንና ግሩፑን ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የሚያስችል መደላደል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በሂደቱ ለተሳተፉ የቦርድ፣የማኔጅመንትና የሰራተኛ ማህበራት ተወካዮችን አመስግነዋል፡፡
በስነ ስርአቱ ላይ የቦርድ አመራር አባላት፣የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተደዳር አጀንሲ ተወካይ፣የግሩፑ ስራ አስፈጻሚዎችና የማኔጅመንት አባላት፣ የሰራተኛ ማህበር ተወካዮች በመሳተፍ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
የቀድሞ ዋና ስራ አስፈጻሚዋን ጉዞ የሚዳስስ ፊልም የቀረበ ሲሆን ከማኔጅመንቱና ከሰራተኛው ለኢንጂነር ህይወት እና ለአዲሱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ስጦታና ማስታወሻ አበርክተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *