ዋና ስራ አስፈጻሚው ከኦፕሬሽንና ከሃብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች ጋር በመሆን ነው ጉብኝት እያደረጉ ያሉት፡፡
በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በመገኘት ከኢንዱስትሪው የማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በኢንዱስትሪው የሚገኙ የተለያዩ ፋብሪካዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አንዳርጌ አያሌው ኢንዱስትሪው የሚገኝበትን ተጨባጭ ሁናቴና ከቶፕ ማኔጅመንት ሊደረግ የሚጠበቀውን ድጋፍ በተመለከተ አብራርተው ውይይት ተደርጓል፡፡
በቀጣይ ጥልቅ ውይይት በቶፕ ማኔጅመንት ደረጃ ተካሂዶ የመፍትሄ ሃሳብ እንደሚቀመጥ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ጉብኝቱ በሁሉም ኢንዱስትሪዎች እንደሚካሄድ የተዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ ያመላክታል፡፡