የኢኢግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አዲስ አበባ ከሚገኘው የአዘር ባጃን ኤምባሲ ጋር በቀጣይ የሁለትዮሽ ትብብርና የስራ ሂደት ላይ ምክክር አደረጉ፤
ሁለቱ አካላት በውይይታቸው ላይ አትኩረው ካነሷቸው ጉዳዩች መካከል በዋነኝነት ኢኢግ ያለውን የመስሪያ ቦታ ፣በስራ ላይ ያሉ የፕላስቲክና ፖሊመር ምርት ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና የእርሻ ማሽነሪና ተቀጽላዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች/ ተጨባጭ ሀብቶች በተሻለና ተወዳዳሪ ሊያደርግ በሚችል አቅም ላይ ለማድረስ በትብብር ከመስራት ባለፈ አዘር ባጃን ባላት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ብሎም የመፈጸም አቅም ለግሩፓችን እና የአፍሪካ መቀመጫ ለሆነችው ኢትዮጵያ ያላትን ልምድና ዕውቀት ለማጋራት ዝግጁ መሆናቸውን አውስተዋል፤
በመሆኑም በቀጣይ ሰኔ ወር በአዘር ባጃን ዋና ከተማ ባኩ በሚካሄድ የንግድ ፎረም ላይ የግሩፓችን የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ባለው ዕድል ላይ እንዲመክሩና ድርጅታቸውን እንዲያስተዋውቁ ከሁለቱም ወገን የሚያመቻቹ ተወካዩችን በማዘጋጀት ወደ ስራ እንደሚገባ፤
በመሆኑም ከዚህ ምክክር በመቀጠል ባሉን ዕድሎች ላይ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ በኢኢግ በኩል በተለይ አገራችን በግብርና ማሽነሪና ተቀጽላዎች፣ በፕላስቲክና ፖሊመር ምርቶች፣ በፓወር ኢክዩፕመንት ምርቶች ሰፊ ገበያ መኖሩንና ይህንን ዕምቅ ፍላጎት ለመድረስ በጋራ መስራታቸው ለሁለቱም አገራት ጠቃሚና ወቅታዊ መሆኑን በውይይታቸው ላይ በአጽንኦት አንስተዋል፤