የፍሬን ሸራ ምርቶችን የበለጠ ለገበያ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ምክክር ተካሄደ።

የፍሬን ሸራ ምርቶችን የበለጠ ለገበያ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ምክክር ተካሄደ።
ምክክሩ የተደረገው በትንትናው እለት በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የአዋሽ አርባ ፍሬን ሸራ ማምረቻ ፋብሪካ በተጎበኘበት ወቅት ነው።
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሪፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ የተመራው የአመራር ቡድን የፍሬን ሸራ ማምረቻ ፋብሪካ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውሮ የተመለከተ ሲሆን ምርቱ አሁን ካለበት የበለጠ ለገበያ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጧል።
የግሩፑን የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ክፍሌ ገ/ማሪያምንና የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴ ያካተተው የአመራር ቡድን የተለያዩ ጉዳዮችን አንስቶ ተወያይቷል።
ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ፋብሪካው በቂ ጥሬ ዕቃዎች ያሉት በመሆኑ ይህንን በመጠቀም በደንብ ለገበያ ተደራሽ ማድረግ ይገባለ ብለዋል፡፡
በኦፕሬሽን ዘርፍ የሚመራ ቡድን በማቋቋም ፋብሪካው ያሉበት ዋና ዋና ተግዳሮቶችን በመለየት መፍትሔ እንዲሰጥም ተብሏል፡፡
የምርት ጥራት ማረጋገጫ ሠርተፊኬት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት በማፋጠን ምርቱን ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ ልይም ምክክር ተካሂዷል፡፡
የዕውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችሉ ስልጠናዎችን መስጠት እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
ፋብሪካው የፒክአፕ፣የሚኒባስ፣የከተማ አውቶብስ፣የቪትስና የሲኖ ትራክ የፊትና የኋላ ፍሬን ሸራን ያመርታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *