በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሁለት ሺህ ባሶች ጥሬ እቃ ግዥ የፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ተከፈተ፡፡
በዚህ አለም አቀፍ ጨረታ ሁለት ድርጅቶች የቴክኒክ ውድድሩን ማለፋቸው ይታወቃል፡፡
ዛሬ ከሰአት በኋላ የሁለቱ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት ያቀረቡት የፋይናንስ ሰነድ መከፈቱን ከኢንዱስትሪው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህ ሳምንት መጨረሻ አሸናፊው ኩባንያ ይፋ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ባሶቹን የሚያቀርበው ለአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ነው፡፡
እነዚህ ባለ ዝቅተኛ ወለል የከተማ አውቶብሶች የአዲስ አበባን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ናቸው፡፡
ኢንዱስትሪው አስፈላጊውን ሂደት በማለፍ በቀጣዩ የበጀት አመት ሁለት ሺህ ባሶችን ወደ ማምረት እንደሚሸጋገር ይጠበቃል፡፡