በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢኩፕመንትስ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጉብኝት ተካሄደ፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር እንዳወቅ አብቴና ሌሎችም የስራ ሃላፊዎችና አማካሪዎች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል፡፡
የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይሉ ጫካ የኢንዱስትሪውን ያለፉት አመታት ጉዞ፣ ተስፋዎችና በሙሉ አቅሙ ለማምረት ተግዳሮት የሆኑባቸውን ጉዳዮች በስፋት አቅርበዋል፡፡
በተያዘው የበጀት አመትም ሰዊቺንግ ሞጁልና ፒኪዩ ማስተር የተባሉ የሃይል ብክነትን ለመከላከል የሚያግዙ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ማምረታቸውን ነው የገለጹት፡፡
ኢንዱስትሪው ካሽ ሪጅስተር ማሽንና ታብሌት ኮምፒወተሮችን ለማምረት የሚያስችል ፋሲሊቲ ያለው በመሆኑ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡
በተለይም በዲዛይን ስራ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች እጥረትና የካሊብሬሽን ማሽን እጥረት ተግዳሮት እንደሆነባቸው አንስተዋል፡፡
የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጉብኝቱ በኋላ እንደገለጹት የጎደሉ ማሽነሪዎችን ለማሟላት እየተደረገ ያለው ጥረት በፍጥነት መጠናቀቅ እንዳለበትና ገበያው የሚፈልጋቸው ሌሎች ምርቶች ላይም በትኩረት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ መራመድ እና ቁልፍ የሆኑ ባለሙያዎች እንዲሟሉ መደረግ አለበትም ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የተገቡ ውሎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባም የገለጹ ሲሆን ጠንካራ ፓርትነር በመመስረት ኢንዱስትሪውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም አመልከተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *