የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፋይናንስ ሪፖርት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የፋይናንስ ሪፖርት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ፡፡
የግሩፑ የቦርድ አባልና የፋይናንስና ኦዲት ንኡስ ቦርድ አባል አቶ አየለ ከበደ እንዲሁም የግሩፑ የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም በተገኙበት ነው ውይይቱ የተካሄደው፡፡
በተለይም የ2013 የፋይናንስ ሪፖርት ትክክለኛ ሆኖ እንዲወጣ የሚያስችል ምክክር ተካሂዷል፡፡
በዋናው መስሪያ ቤትና በስሩ በሚገኙት 9ኙ ኢንዱስትሪዎች ለአመታት የተንከባለሉና ያልጠሩ ሂሳቦችን ለማጥራትና ትክክለኛ የፋይናንስ ቁመናን ለመላበስ ተከታታይ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡
የቀድሞው ሜቴክን ሂሳብ በመዝጋት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን ሂሳብ በአጭር ጊዜ አዲስ መልኩ ማስጀመር ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የ2013 የሂሳብ ስራው የደረሰበት ደረጃ በዝርዝር ቀርቦ በጥልቀት የተገመገመ ሲሆን ቀሪ ስራዎች መጠናቀቅ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ የፋይናንስና ኦዲት ንኡስ ቦርድ አባል የሆኑት አቶ አየለ ከበደ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የዋና መስሪያ ቤት የፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጆችና የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጆች እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የኢንዱስትሪ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *