በስኳርና በብረታ ብረት ምርት ዘርፍ የተሰማሩ ፋብሪካዎች በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኘውን የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ኢንዱስትሪን ጎበኙ፡፡
የከሰም ስኳር ፋብሪካ ፣የወንጂ ስኳር ፋብሪካ እና የኮምቦልቻ ብረታ ብረት ምርቶች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሥራ ኃላፊዎች ናቸው በጉብኝቱ የተሳተፉት፡፡
ከጉብኝቱ በተጨማሪ በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂደዋል፡፡
የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ላቀው አስማረ ፣ የኢንዱስትሪው አመራሮች እና የግሩፑ የቢዝነስና ዴቨሎፕመንት የሥራ ኃላፊዎች ኢንዱስትሪው ስለሚገኝበት ደረጃ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በቀጣይነት የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ምርቶችና አገልግሎቶችን በጥራት እና በጊዜ ለማቅረብ የሚያስችሉ ሂደቶች ላይ መግባባት ተችሏል፡፡
ጉብኝዎችም ኢንዱስትሪው ያለው አቅም የመለዋወጫ ክፍተታቸውን እንደሚሞላቸው የገለጹ ሲሆን የዋጋ እና የአቅርቦት ጉዳይ ሊሻሻል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች ሁለቱ ተቋማት በጋር በሚሰሯቸው ስራዎች ላይ በቅርቡ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡