በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ደም የመለገስ መርሐ ግብር ተከናወነ፡፡

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ደም የመለገስ መርሐ ግብር ተከናወነ፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋናው መ/ቤት፣የኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ: የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትራ እና የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ አመራርና ሰራተኞች ናቸው በመርሃ ግብሩ የተሳተፉት፡፡
ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን እንዲሁም ለወገናችን በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ ፕሮግራሙ ተካሂዷል፡፡
በመርሐግብሩ ላይ የተሳተፉት አመራሮችና ሰራተኞች እንደገለጹት ሃገራችን እንዲህ ባለ አስጨናቂ ጊዜ ላይ እያለች ሁሉም ሰው ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆም አለበት ያሉ ሲሆን፤ ደም በመለገሳቸውና በሃገራዊ ጉዳይ ላይ ተሳትፎ በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ህይወታቸውን ሰውተው ለሀገር ደጀን ለቆሙት ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ለወገኖቻችን ደማችንን መለገሳችን አብሮነታችንን የሚያሳይና ከጎናቸው መቆማችንን የሚመሰክር ተግባር ነውም ብለዋል፡፡
ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ነው ደም የመለገስ መርሐግብር የተከናወነው፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ላይ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ሲሆን ፣ከዚህ ተልዕኮው በተጓዳኝ በሀገራዊ፣ አካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳይች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል፡፡
መርሐግብሩ በቀጣይም በስሩ ባሉት ኢንዱስትሪዎችም ይቀጥላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *