ኢ.ኢ.ግ የአይሶ (9001:2015) የአሰራር ሰርተፌኬት ፊርማ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር ፈረመ፡፡

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሚያመርታው ምርቶች እና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በጥራት ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናገሩ፡፡
በዛሬው እለት ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎችን ያቀፈው የዋና መስሪያ ቤት የአይሶ (9001:2015) የአሰራር ሰርተፌኬት ፊርማ ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር ተፈርሟል፡፡
ይህ የፊርማ ስምምነት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና መስሪያቤት አይሶ(9001:2015)አሰራር ሰርተፊኬት ለማግኘት የሚያስችለው ነው።
ግሩፑን በመወከል የኢ/ኢ/ግ/ ዋ/ስ/አስፈጻሚ ምስጋኑ አርጋ(አምባሳደር) እንዲሁም የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋ/ዳይሬክተር ዶ/ር መሠረት በቀለ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
በስነ-ስርአቱ ላይ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የምናመርታቸው ምርቶች ደረጃ እንዲወጡላቸው በማድረግ ወደ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲገቡ እንፈልጋለን፡፡ ለዚም መሳካት እቅድ ነድፈን የምርቶቻችንን ጥራት አስጠብቀን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንሰቲትዩት ዋ/ዳይሬክተር ዶክተር መሠረት በቀለ ይህ ስምምነት የጥራት ቁጥጥር ስርአቱ በተግባር እንዲታይ የሚረዳ ሲሆን በተባለው ጊዜ ገደብ ተጠናቆ እንዲያልቅ የሁሉም አመራሮች ከፍተኛ ሚና ያስፈልጋል ብለዋል።
እስካሁን ድረስ በግሩፑ ስር ካሉ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ የአይሶ ሰርተፊኬት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል።
የአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ፣ፓወር ኢኩፕመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፣ የአዳማ ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፣ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና የኤሌክትሮኒክ ኢክፑመንት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ይህን የአሰራር ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ለማግኘት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ናቸው።
ይህ አሰራር ሰርተፊኬት ተቋማት የሚያከናዉኑትን ተግባር ጊዜውን የጠበቀ እንዲሆንና ዘመናዊ አሰራር ስርአትን ለመዘርጋት የሚያስችል ነው።
እንዲሁም ከሌሎች ሀገር አቀፍ ተቋማት ጋር ለመስራት ግሩፑ እያካሄደ ላለው ጥረት የአይሶ ሰርተፊኬት ሂደት ሚናው የላቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *