ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሱማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የድህረ-ሽያጭ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ።

ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በሱማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የድህረ-ሽያጭ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት አስቀመጠ።
በሁነቱ ላይ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የልዑካን ቡድናቸው፣ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ኡመር እና የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ተገኝተው በጋራ የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል።
እንደሚታወቀው ክልሉ ከአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የግብርና ማሽነሪዎችን በመግዛት ግንባር ቀደም ደንበኛ መሆኑ ይታወቃል።
ይህ የድህረ ሽያጭ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለግብርናው ስራ ማሽነሪዎችን ውጤታማ በማድረግ ምርታማነትን ለመጨመር ወሳኝ በመሆኑ ግሩፑና ክልሉ በትኩረት ሰርተው ለአገልግሎት ለማብቃት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *