ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ(ኢኢግ)፡- አትዮ – ኢንጂነሪንግ ግሩፕ “ኢንቬስት ኦሪጅንስ” በሚል ስያሜ የኢትዮጵያ የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ባዘጋጀው እና በርካታ የሃገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር አምራቾች ፤አስመጪዎችና አከፋፋዮች በተገኙበት አለም አቀፍ ሲምፖዚየምና ኢግዚብሽን ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
በዛሬው እለት በሳይንስ ሙዚየም በተከፈተው እና እስከ ነገ በሚቆየው በዚህ ፕሮግራም ላይ ግሩፑ ምርቱን እና አገልግሎቱን ለተሳትፊዎች እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የግሩፑ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በሲምፖዚየሙ እና ኢግዚብሽኑ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ሲምፖሲ,ዚየሙ በርካታ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ተቋማትን፣ ውሳኔ ሰጪዎችን፣ ፓናሊስቶችን፣ የኤግዚቢሽን ተሳታፊዎችን ፤መንግሥታዊ የሆኑና ያልሆኑ የኢንቨስትመንት ኩባንያዎችን እና ሌሎችንም በአንድ መድረክ ያሰባሰበ ነው፡፡ ከኢንቨስትመንት ዘርፍ ባለሙያዎች በተጨማሪ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችም የፎረሙ ተሳታፊዎች ናቸው።
በተለይ በፎረሙ ላይ ከ300 በላይ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ተዋንያን ያሳተፈ ሲሆን፣ ፕሮገራሙ በኦንላይን እየቀረበ ይገኛል፡፡
“ኢንቬስት ኦሪጅንስ” በቤቶች ግንባታ፣ በጤና፣ በትምህርት፣በማኑፋክቸሪንግ፣በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም ሆቴል፣ ቱሪዝምና መስተንግዶ ላይ በትኩረት እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

