አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተመደቡ፡፡

አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተመደቡ፡፡
የግሩፕ ስራ አመራር ቦርድ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ፣ ከዋና ስራ አስፈጻሚ በተጨማሪ ሁለት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችንም መድቧል፡፡
አቶ መሃመድ ጀማል ሸሪፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሃላፊ እና ወ/ሮ መሰረት ደስታ ገ/የሱስ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ የምርምርና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ሃላፊ በመሆን ተመድበዋል፡፡
በግሩፑ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በዶክተር አብረሃም በላይ ተፈርሞ በወጣው ደብዳቤ መሰረት የስራ ሃላፊዎቹ ከጥር 7 ቀን 2015 አ/ም ጀምሮ ነው የተመደቡት፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ድኤታ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሾማቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *