እንኳን ለጌታ እየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ!!
ተቋማችን ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከኪሳራ በመውጣት በያዝነው አመት 70 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ትርፍ አስመዝግቧል፡፡
የውጭ ምንዛሪ እና የግብአት እጥረት ቢያጋጥመንም በሰራናቸው የሪፎርም ስራዎች፣ የውስጥ አቅማችንን አሟጠን በመጠቀም ፤ አዳዲስ አመራሮችን በመመደብ፣ እና መላው ሰራተኛችንን በማረባረብ የተመዘገበ ትርፍ ሲሆን ይህንን ጥረታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡
ግሩፑን በአዲስ አደረጃጀት በማደራጀት፤ አዲስ መዋቅር በማዘጋጀት ለተሻለ ከፍታና ትርፋማነት በመስራት ላይ ነን፡፡
በጆይንት ቬንቸርና በሌሎችም የአጋርነት ስልቶች በትራክተር፣ በፓምፕ፣በሶላር፣ በአውቶብስና በኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በመስራት አዳዲስ ፋብሪካ በአጠረ ጊዜ ውስጥ አውን እናደርጋለን፡፡
ከውጭ የሚገቡ ትላልቅ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ምርቶችን በሃገር ወስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሪን ከማዳን በተጓዳኝ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ እንዲገኝ እየሰራን እንገኛን፡፡ በሁሉም ኢንዱስትሪዎቻችን ውጤታማ ስራዎችን እያከናወንን ሲሆን ጥረታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ግሩፑ ለያዛቸው ውጥኖች መሳካት የስራ አመራር ቦርዱ ለተጫወተው የአመራር ሚና በራሴና በማኔጅመንቱ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፤ ለመላው ሰራተኞች ፣ ደንበኞቻችንና ባለድርሻ አካላት መልካም በአል እንዲሆን እየተመኘሁ በቀጣይም እንደተለመደው ከጎናችን እንድትቆሙ በዚህ አጋጣሚ የአክብሮት ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
መልካም በአል!!
ምስጋኑ አርጋ (አምባሳደር)
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ