የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች ደብረ ብርሃን የሚገኘውን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎበኙ፡፡

ኢንዱስትሪው የሃገሪቱን የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ፍላጎት ለማሟላት የተቋቋመ ነው፡፡
በዋነኛነት የኮንስትራክሽን ማሽነሪ የሆኑትን ሎደር፣ ስካቫተር፣ ክሬሸርና ባቺንግ ፕላንት የሚያመርት ኢንዱስትሪ ነው፡፡
እንዲሁም ለግንባታ ስራዎችን የሚውሉ ዘመናዊ የፎርም ዎርክ፤ስካፎልዲ ምርቶችን ያመርታል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እንዳሉት ሀገሪቱ በመገንባት ሂደት ላይ በመሆኗ የኢንዱስትሪው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
ኢንዱስትሪው ትልቅ አቅም ያለው በመሆኑ ያሉትን ውሱንነቶች በመቅረፍ በሙሉ አቅም እንዲያመርት ማድረግ ይገባል፡፡
ከውጭ የሚገቡትን ማሽነሪዎች በሃገር ውስጥ እንዲመረቱ የማድረግ አቅም እንዳለውም ተገልጿል፡፡
ካይዘን ማስፋፋት፤ ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠርና፤ ሰራተኛውን ማሳተፍ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ስራዎች ተብለዋል፡፡
ኢንዱስትሪውን ውጤታማ ለማድረግ በተለያዩ መልኮች ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በጥምረት ለመስራት እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡
ከቱርክና ከጣሊያን ኩባንያዎች ጋር በቴክኖሎጂ አቅርቦትና በአጋርነት ስራዎችን ለመስራት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የግሩፑ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎችና የማኔጅመነት አባላት ተሳትፈዋል፡፡
በአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘው የቤሪንግ ፋብሪካ ያለበት ደረጃም ተጎብኝቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *