በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ደም የመለገስ መርሐ ግብር ተከናወነ።

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ደም የመለገስ መርሐ ግብር ተከናወነ።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋናው መ/ቤት፣የኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪና እና የብረታ ብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ አመራርና ሰራተኞች ናቸው በመርሃ ግብሩ የተሳተፉት ።
የዛሬው መርሃ ግብር ለአምስተኛ ዙር ደማችን ለወገናች በሚል መሪ ቃል ተከናውኗል።
በመርሐግብሩ ላይ የተሳተፉት አመራሮችና ሰራተኞች በመልዕክታቸው ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት ደም በመለገስ ማዳን ስለሚቻል ብሎም እናቶች በወሊድ ወቅት የሚያጋጥማቸውን ከፍተኛው የደም መፍሰስ ለመተካት ስለሚጠቅም ለዚህም ተሳትፎ በማድረጋቸው ደስታቸውን ገልፀዋል።
ግሩፑ በበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲሰርፅ የሀገራችን መልካም ባህል አካል እንዲሆን በተቋም ደረጃ በማስተባበር ላበረከተው አስተዋፅዎ ከኢትዮጵያ ደምና ቲሹ ባንክ አገልግሎት የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ በኢንዱስትሪዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሀገራችን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለምታደርገው ጉዞ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ሲሆን፣ከዚህ በተጓዳኝ በሀገራዊ፣አካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *