በኢትዮ ኢንጂነሪንግ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ስር የሚገኘውን የአዋሽ አርባ ፍሬን ሸራ ማምረቻ ፋብሪካ በደንበኞችና በሚዲያ አካላት ተጎበኘ።

በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ትላልቅ ተቋማት እና በአውቶሞቲቭ ዘርፍ ፕሮግራሞችን የሚሠሩ የሚዲያ አካላት የፍሬን ሸራ ማምረቻ ፋብሪካውን ጎብኝተዋል።
የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ላቀው አስማረ የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በደንበኝነት አብረውን እየሠሩ ያሉ ተቋማት የአመራረት ሂደታችንን በአካል በማየት የበለጠ መተማመን እንዲኖራቸው ለማድረግና የሚዲያ አካላት በየፕሮግራሞቻቸው ለእምቅ ደንበኞቻችን መረጃውን የማድረስ ሙያዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ነው ብለዋል።
የሀገራችን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከሚፈልጉት አንዱ የአውቶሞቲቭ መለዋወጫ በመሆኑ የውጭ ምንዛሪን ለማዳንና ኤክስፖርት ለማድረግ በትኩረት እንደማሰራ የገለፁት የግብይትና ሽያጭ መምሪያ ሀላፊ አቶ ታደሰ ጉርሙ ናቸው።
 ከተለያዩ ትራንስፖርት ተቋማት የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በበኩላቸው ለአውቶሞቲቭ ዘርፉ ማደግ አንዱ የእነዚህ መለዋወጫዎች በበቂ ደረጃ መኖር ነው።የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምርት የሆነው የአዋሽ አርባ ፍሬን ሸራ ማምረቻ ፋብሪካ የምርት ሂደቶቹ በጥንቃቄ የሚሄዱ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።


 በጉብኝቱ የተሳተፉ የሚዲያ አካላት እንደ ሀገር የሚያኮራ ነገር ተመልክተናል በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ መሆኑን ተከትሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት ስለሚችል እኛም በማስተዋወቁ የድርሻችን እንወጣለን ብለዋል።
ፋብሪካው በዓመት 669,000 የሲኖ፣የከተማ አውቶብሶች፣የዳንጎቴ ትራኮች፣የሚኒባሶች፣የቪትዞች፣የሃይሩፍ እና ቢሾፍቱ ፕክ አፖች የሚያገለግሉ ፍሬን ሸራዎችን ያመርታል።
    
ፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት፣የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት፣የበከልቻ እና ጥቁር አባይ ትራንስፖርት አመራርና ባለሙያዎች በጉብኝቱ ተሳትፈዋል።
አውቶሞቲቭ ታይም፣አዲስ አውቶሞቲቭ፣እንደርሳለን(በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬትና ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ላይ የሚሠሩ የአውቶሞቲቭ ፕሮግራም አዘጋጆች )እንዲሁም ኤፍ ኤም 95.1 እና ኤፍ ኤም 106.1 ሚዲያዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *