በግሩፑ ስር የሚገኙት ዘጠኙም ኢንዱስትሪዎች ከምርት፣ከሽያጭ፣ከተሰብሳቢ እና ከሌሎችም ተግባራት አንጻር በቀጣይ ስድስት ወራት የሚያከናውኗቸውን ተግባራት ከልሰው አቅርበዋል፡፡
እቅዱን ለመከለስ ታሳቢ ያደረጓቸውን ታሳቢዎች መሰረት በማድረግ የኢንዱስትሪንና የግሩፑን ትርፋማነት ሊያስቀጥል የሚችል እቅድ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
የውስጥ አቅማቸውን አሟጠው በመጠቀም ትርፋማነትን ለማስቀጠል እንደሚሰሩ የገለጹ ሲሆን አዳዲስ ምርቶችን አምርቶ ወደ ገበያ ለማስገባት እና ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በጋራ ለመስራት የተጀመሩ ጥረቶች ከዳር እንዲደርሱ እየሰሩ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡
በቀረበው እቅድ ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵ የራሷ ብራንድ ይገባታል የሚለው ራእይ እንዲሳካ የሎካላይዜሽን ስራ አስፈላጊነት ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
የኢንዱስትሪዎች የርስ በርስ ትስስርን በማጎልበት እና የፈጠራ ስራን በማከል መስራት እንደሚገባም ውይይት ተካሄዶበታል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በተለይ አዳዲስ ምርቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ወጪ ቆጣቢ ሆኖ በመስራት የወጪ ቅነሳ ስራ ላይም በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡የውስጥ ኦዲት ቁጥጥር ስርአቱን በመጠቀም አላስፈላጊ ወጪን መከላከል እንደሚገባ በመጠቆም፡፡
ግሩፑ የተሰማራበትን ዘርፉን የመምራት፣ገበያ ማረጋጋት እና ተኪ ምርቶችን ማምረት ላይ በትኩረት መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡