በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና መ/ቤት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

መጋቢት 5/2016 ዓ.ም- ( ኢ.ኢ.ግ ) አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) “ሴቶችን እናብቃ ልማትንና ሠላምን እናረጋግጥ “ በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች የነበረባቸውን ከፍተኛ ጫና እና ኃላፊነት ታሳቢ በማድረግ ግሩፑ ባካሄደው ሪፎርም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል፤ እንደ ግሩፕ የሴት ሰራተኞች ሚናን ከፍ ለማድረግ ከዚህም በላይ ጥረቶች እንደሚደረጉ ገልፀዋል ፡፡
የግሩፕ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት ደስታ ግሩፑ ለሴት ሰራተኞች የፈጠረውን መልካም ዕድሎች የበለጠ ለመጠቀም ዝግጁ መሆንና መትጋት ከሴቶች የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም በስራ እና በተግባርም ተግቶ መገኘት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አገልግሎት ኃላፊ ወ/ት በረከት አሰፋ እንደ ግሩፕ የሴቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የተሰራ ስራ አርኪ መሆኑን በመግለፅ የሃላፊነትን ሚናቸውን የተወጡ በየደረጃው ላሉ የግሩፑ አመራሮችን አመስግነዋል፡፡
የህጻናት ማቆያዎች ላይ ጥሩ ስራ ለሰሩ፣የኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራሞችን በመቅረጽ ድጋፍ ላደረጉ ፣የሴት ሰራተኞችን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ጥሩ ውጤት ላሳዩ አራት ኢንዱስትሪዎች የዕውቅና ሰርትፊኬት ተበርክቷል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በግሩፑ ሴቶችን በማብቃት እና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የግሩፑ ከፍተኛ አመራሮችም  እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *