ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና ኦ-ፕሮድዮስ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የኦ-ፕሮድዮስ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ማርታ በላይ ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡
ሁለቱ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በሁሉን አቀፍ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ስሌይማን ደደፎ የሃገራችንን የገበያ ፍላጎት ለማሟላት የሁለቱ ተቋማት ጥምረት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣የውጭ ምንዛሪን በመተካት እና የቴክኖሎጂ ትብብር በመፍጠር ረገድ ሁለቱ ተቋማት ተቀናጅተው ይሰራሉ ብለዋል፡፡
የኦ-ፕሮድዮስ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ማርታ በላይ በበኩላቸው እንደገለጹትም በአምራች ዘርፍ ሰፊ ልምድ ካለው ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በጋራ መስራታችን በማሽን መለዋወጫ እቃ አቅርቦት፣በቴክኖሎጂ ውጤቶች ትግበራ እና በቴክኒክ ትብብር በጋራ እንድንሰራ ምቹ አጋጣሚን ይፈጥራል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በስሩ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎችን ያቀፈ የልማት ድርጅት ሲሆን ኦ-ፕሮድዮስ ኢንቨስትመንት ግሩፕም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቢሮ ስር የሚገኝ በስሩ ስድስት ኢንዱስትሪዎችን ያቀፈ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *