የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ሰራተኞች 21ኛው ሳፍሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ. ሩጫ ላይ ተሳተፉ።

በታላቁ ሩጫ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለ 21ኛ ዙር “የሴቶችን አቅም እንደግፍ ፤ለውጥን እናፋጥን “በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።
በውድድሩ አትሌቶች፣ የ11 ሀገራት እንስት አምባሳደሮች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ 15 ሺህ የጤና ሯጮች ተሳትፈዋል።
ሩጫውን ያስጀመሩት የውድድሩ የክብር እንግዶች የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የአዲስ አበባ የባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን እንዲሁም የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ መልካሙ ተገኝ ናቸው፡፡
መነሻ እና መድረሻው አትላስ ሆቴል አካባቢ ባደረገው የሩጫ ውድድር ላይ ከ15 ሺህ በላይ ሴቶች ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *