ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የሶማሌ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ የእርሻ መሳሪዎች ሽያጭ ውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የግሩፑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳር ሱሌይማን ደደፎ እና የሶማሌ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር  አብዱልቃድር ኢመን ፈርመዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረት በግሩፑ ስር የሚገኘው የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ 50 ዋይቲኦ ትራክተሮችን፣50 ማረሻ፣50 መከስከሻና 5 ኮምባይነሮችን አምርቶ ያቀርባል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የድህረ ሽያጭ አገልግሎት መስጠትም  በስምምነቱ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡
የሶማሌ ክልል በግሩፑ ስር ለሚገኘው የአዳማ ግብርና  ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ዋና ደንበኛ ሲሆን በተለያዩ ዙሮች የእርሻ መሳሪያዎችን እየወሰደ  ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *