ስምምነቱን የፈረመው ከሀገር በቀሉ ፍራንኩን ኢት አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ጋር ነው፡፡
ስምምነቱን የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የፍራንኩን ኢት አውቶሞቲቭ ኢንጅነሪንግ ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ ፍራንቼስኮ ቪሎሜ ጁሴፔ ተፈራርመውታል።
በዚሁ ስምምነት መሰረት ሃገር በቀሉ ፍራኩን ኩባንያ በኤስ ኬ ዲ የሚመረቱ የሃምሳ ዳም ትራኮች ግብአት ለቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማመምረቻ ኢንዱስትሪ በማቅረብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሸከርካሪዎቹ ተመርተው ለገበያ ይቀርባሉ፡፡
ፍራንኩን በሚል ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሃገር በቀል ከባድ መኪኖች በማምረት የሚታወቀው ፍራኩን ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነቱን የሚያጠናክርበት ስምምነትም ተፈርሟል፡፡
በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በቴክኖሎጂ፣በሰው ሃይል ስልጠናና በተለያዩ መንገዶች በመተሳሰር ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡


