ኤክስፖውን የኢፌድሪ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በይፋ ከፍተውታል።
በኤክስፖው ላይ በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኙት ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።
ግሩፑ የኤሌክትሪክና የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች፣ የአውቶሞቲቭ ምርቶች፣የኮንስትራክሽን፣የግብርና፣ የብረታብረት ምርቶች፣የፕላስቲክና ኮምፖሳይት ምርቶችን ይዞ በስፋት እያስተዋወቀ ይገኛል።
የመክፈቻ ስነ-ስርአቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶች በሃገር ውስጥ እንዲመረቱ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ሰፊ አስተዋፅዎ አበርክቷል።
ለዚህም መንግስት በፖሊሲና በአሰራር ሰፊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
በኤክስፖ ላይ ከ 210 በላይ ኩባንያዎች እየተሳተፉ ሲሆን ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከነዚህ ኩባንያዎች እና ከጎብኚዎች ጋር የመተዋወቅና አብሮ የመስራት እድል እንደሚፈጥርለት ይጠበቃል።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ምርቶች በጠ/ሚ አብይ አህመድ ፣ በክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና በተለያዩ ጎብኝዎች እየታየ ይገኛል።
ኤክስፖው እስከ ግንቦት 5 ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።









