ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ እንዲመረቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠው፡፡

ሽልማቱ የተበረከተው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡
ኤክስፖው ሲጠናቀቀ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ስር የሚገኙ ዘጠኝ ኢንዱስትዎች ምርታቶቻቸውን አስተዋውቀዋል፡፡
የግሩፑ ምርቶች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣በክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣በሚኒስትሮች እና በተለያዩ ጎብኝዎች ታይቷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ለግሩፑ እውቅና የተሰጠው ሲሆን ሲሆን የሳፋሪ የቱሪስት መኪና የሰራውን ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪም በተመሳሳይ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡
በሚሊኒየም አዳራሽ ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ 200 በላይ አምራች ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን አቅርበውበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *