ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አሰፈጻሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ ናቸው፡፡
በስምምነቱ መሰረት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያ፣ የኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ትራንስሚሽኖችንና ሌሎች ምርቶችና መለዋወጫዎን ያቀርባል፡፡
እንደዚሁም በግሩፑ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ምርቶችና አገልግሎቶችን ለማቅረብና ተቀራርበው ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
የሁለቱ ተቋማት ባለሙያዎች በቴክኒካዊ ጉዳዮች ፣በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ በመስራት የሃገሪቱ የሃይል ምርትና ስርጭት እንዲያድግ ይሰራሉ፡፡
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመስራት ሃገሪቱ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት ይችላሉ ብለዋል፡፡
በሁሉም ዘርፎች የሃገርን ምርት ማበረታታት ካልተቻለ የሃገር እድገት እንደማይጣ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በበኩላቸው ስምምነቱ የሃገርን ጥቅም እንደሚያስከብር ገልጸው በአዲስ አመራር በሪፎርም ሂደት ውስጥ ከሚገኘው ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የስራ ሃላፊዎቹ ስምምነቱ እውን እንዲሆን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ላበረከተው አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *