ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የዳኔሊ ግሩፕ የአፍሪካ አጋርነት ፕሮጀክት ፕሬዝዳንት ዳኒሎ ድሮሊኒ ናቸው፡፡
የነቀምቴ ስቲል ፕሮሰሲንግ ፕላንት ፕሮጀክት ከሃገራዊ ለውጡ በፊት 50 ሚሊየን ዮሮ ወጥቶበት ወደ ተግባር ሳይገባ የቆየ ፕሮጀክት ነበር፡፡
ፕሮጀክቱ 300 ሺህ ቶን ብረት የማምረት አቅም ያለውና የተለያዩ ሪባርና የብረት ፕሮፋይሎችን ለማምረት ያስችላል ተብሎ የተጀመረ ነው፡፡
ለአመታት ቆሞ የቆየውን ፕሮጀክት ወደ ስራ ለማስገባት የቴክኖሎጂው አቅራቢ ከሆነው ኩባንያ ጋር ነው ስምምነቱ የተፈረመው፡፡
በስምምነቱ መሰረት የኩባንያው ባለሙያዎች የኢንስፔክሽንና የማማከር ስራዎችን በማከናወን እና ተከታታይ ስራዎችን በማከናወን ፕሮጀክቱ ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል፡፡
የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ለሃገሪቱ የብረት ምረት አቅረቦት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡




